ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለፉት 25 ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች በኢትዮጵያ ስኬት ተመዝግቧል ይላሉ
Your browser doesn’t support HTML5
የደርግ መንግሥት ከሥልጣን ተወግዶ ኢሕአዴግ ሥልጣን ላይ የወጣበት 25ኛው የብር ኢዮቤልዩ በዐል፣ በተለያዩ ሥነ ሥርዓቶች በመከበር ላይ ይገኛል። በዚሁ መነሻ፣ ባለፉት 25 ዓመታት በተለያዩ ዘርፎች ኢትዮጵያ ውስጥ ስኬት ተመዝግቧል ይላሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ። ተቃዋሚዎች ደግሞ፣ የኢሕአዴግ 25 ዓመት የሥልጣን ዘመን፣ በተለይም በፖለቲካው መስክ፣ ያለ ውጤት የባከነ መሆኑን ይናገራሉ።