የቀድሞዋ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን ያለጥርጥር የፓርቲያቸውን ውክልና ወደ ሚያስገኝላቸው ደረጃ ቀርበዋል

Your browser doesn’t support HTML5

በዩናይትድ ስቴትስ በኬንታኪ እና ኦረጎን የተካሄዱ ቅድመ ምርጫዎች፥ የቀድሞዋ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂላሪ ክሊንተን ያለጥርጥር የፓርቲያቸውን ውክልና ወደ ሚያስገኝላቸው ደረጃ አቅርቧቸዋል። በመጪው ዓመት ህዳር ከሪፐብሊካኑ ተወካይ ዶናልድ ትራምፕ ጋር በሚካሄደው ከባድ ፉክክር አሸናፊው ማን ሊሆን እንደሚችል መተንበይ አስቸጋሪ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ግን የተሻለ እድል እንዳላቸው ብዙዎች ይናገራሉ።