ኬንያ ካምፖችን ለመዝጋት ብታቅድም የስደተኞች መብት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተንታኞች ያሰምራሉ

Your browser doesn’t support HTML5

ኬንያ ባለፈው ሳምንት ሁለት የስደተኞች መጠለያ ካምፖችን  እንደምትዘጋ ስትገልጽ፣ ለዚህም ምክንያቷ የፀጥታ ስጋት እንደሆነ ማመልከቷ አይዘነጋም። አንዳንድ ተንታኞች፣ ከውሳኔው ጀርባ ሌላ ምክንያት መኖሩን ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ፣ የጸጥታ ስጋት መኖሩን ይስማሙና፣ የስደተኞች መብት ግን ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ያሰምሩበታል።