በካኩማ እና ዳዳብ የሚገኙ የኬንያ የስደተኞች ጉዳይ ቢሮዎች ዝግ መሆናቸዉን ስደተኞች ይናገራሉ

Your browser doesn’t support HTML5

የኬንያ መንግስት በዳዳብና ካኩማ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚገኘውን መስሪያ ቤት መዝጋቱን በጣቢያው የሚኖሩ ስደተኞች ተናገሩ። ስደተኞቹ እንደሚሉት የጣቢያው አስተዳደር የሆነዉ የኬንያ የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ ቅርንጫፍ ከባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ አንስቶ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት አቁሟል።