በምዕራብ ወለጋ ዞን ከፖሊስ ድብደባ ጋር በተያያዘ አንድ ተማሪ መሞቱን የከተማዋ ነዋሪዎች ይገልጻሉ

Your browser doesn’t support HTML5

በምዕራብ ወለጋ ዞን ነጆ ከተማ ውስጥ ባለፈው ዕሁድ ሌሊት ከፖሊስ ድብደባ ጋር በተያያዘ አንድ ተማሪ መሞቱን የከተማዋ ነዋሪዎች ለኦሮምኛ ፕሮግራም ክፍል ባልደረባ ለጃለኔ ገመዳ ተናግረዋል። ​​የነጆ ከተማ አስተዳደር ግን ተማሪው የሞተው በሕመም ምክንያት መሆኑን ሐኪም አረጋግጧል ይላል። ​ በሌላ በኩል፥ ቤተሰብ የታሠሩ አባላቱን ማየት እንዳልቻለና ከከተማይቱ በፖሊሶች ተይዘው የተወሰዱትም የት እንደደረሱ እንደማያውቅ ይገልጻል።