የሙሩሌ ጎሣ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል ጥቃት የፈጸሙት በመንግሥት ድክመት ነው ሲል መኢአድ ከሰሰ

Your browser doesn’t support HTML5

ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሙሩሌ ጎሣ ታጣቂዎች በጋምቤላ ክልል ጥቃት የፈጸሙት በመንግሥት ድክመት ነው ሲል የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ መኢአድ ከሷል። ፓርቲው ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ፥ መንግሥት ለዜጎቹ ተገቢውን ጥበቃ አላደረገም ብሏል። የመንግሥት ባለሥልጣናት ሰሞኑን በሰጧቸውአስተያየቶች እንደዚህ ዓይነቶቹን ወቀሳዎች ሲያስተባብሉና ተጨባጩን ሁኔታ እንደማያንፀባርቁ ሲገልጹ ቆይተዋል።