ከአራት መቶ በላይ የሚሆኑ አሶሳ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች ክስ መመስረታቸው ታወቀ

Your browser doesn’t support HTML5

ከአራት መቶ በላይ የሚሆኑ አሶሳ አካባቢ የሚኖሩ አርሶ አደሮች በፌደራል ትምሕርት ሚኒስቴርና በቤንሻጉል ክልል ምክር ቤት ላይ የፍትሐቤር ክስ መመስረታቸው ታወቀ። ለክክልሉ ምክር ቤት መጥሪያ ሊሰጡ የሄዱት የአርሶ አደሮቹ ተወካይ ተይዘው መታሰራቸውም ይሰማል። የክልሉን ምክትል አስተዳዳሪ እና የቤንሻንጉል ጉምዝ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ሊቀመንበር በጉዳዩ ላይ ለማነጋገር የተደረገው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።