ድህነትን ለመቀነስ ባልተደራጁና ባልተረጋጉ ገበያዎች ንግድና ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት

Your browser doesn’t support HTML5

በዓለም የገበያ ስርዓት በአግባቡ የተደራጀ የምጣኔ ስርዓት እንዲሁም ሰላምና መረጋጋት ወሳኝ ናቸው። በተለይ የዓለማችን 2.5 ቢሊዮን ህዝብ በሚኖርባቸው ድሃ ሀገሮች የገበያ ስርዓትና የፖለቲካ አለመረጋጋት ነጋዴዎችና ባለሀብቶችን ያሼሻሉ። መንግስታዊና የግል ዘርፍ ባለሙያዎች ይሄን ችግር እንዴት በጋራ ሊያሻሽሉት እንደሚችሉ ባለፈው ሳምንት በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው የዓለም ባንክና የዓለም የገንዘብ ድርጅት ጉባዔ ውይይት ተደርጎበታል።