ጋምቤላ ውስጥ 140 ሰው ተገደለ

Your browser doesn’t support HTML5

ድንበር ተሻግረው ጥቃቱን ያደረሱት የመሪሌ ጎሣ አባላት ናቸው ሲል የኢትዮጵያ መንግሥት ከስሷል። ከመቶ በላይ ሕፃናት ተጠልፈው ተወስደዋል። ደቡብ ሱዳንን በሚያዋስነው የኢትዮጵያ ምዕራባዊ ድንበር አካባቢ ታጣቂዎች 140 ሰዎችን መግደላቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል። ድንበር ተሻጋሪ ጥቃቱ ጋምቤላ ውስጥ የደረው በመሪሌ ጎሣ ታጣቂዎች ዓርብ፤ ሚያዝያ 7/2007 ዓ.ም. እንደሆነ የመንግሥቱ መግለጫ አመልክቷል።