ጋናና ቶጎ ቀጣዮቹ የአሸባሪዎች ኢላማ መሆናቸውን ሾልኮ የወጣ ሰነድ አመለከተ

Your browser doesn’t support HTML5

በማሊ፣ በቡርኪና ፋሶና በአይቮሪኮስት ሆቴሎች ላይ የአሸባሪ ጥቃቶች ከተደጋገሙ ወዲህ ምዕራብ አፍሪቃ በተጠንቀቅ ሁኔታ ላይ ትገኛለች። አሁን ደግሞ ሾልከው የወጡ የጸጥታ ጉዳይ ሰነዶች እንዳመለከቱት ጋናና ቶጎ ከዐል-ቓዒዳ ጋር የተሳሰረው ጽንፈኛ ቡድን ቀጣዮቹ ኢላማዎች ናቸው። የጋና ፕረዚዳንት ጆን ማሀማ የሀገሪቱ እዝብ እንዲረጋጋ መክረዋል። የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ፍራንሲስካ ካክራ ፎርሶን ከአንካራ የላከችውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ ታደርሰናለች።