“ዐዋጁ ተሰርዞ ውይይት ሊደረግበት ይገባል” አቶ ሙላቱ ገመቹ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ምክትል ሊቀ መንበር
Your browser doesn’t support HTML5
የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ቀደም ሲል ያጸደቀው የከተሞች ዐዋጅ ሦስት አንቀጾች መሰረዙ የሚያመጣው አዲስ ነገር እንደማይኖር፣ ሕዝቡ ስላልተቀበለው ሙሉ በሙሉ መሰረዝ አለበት፤ "ጠቃሚ ኾኖ ቢገኝ እንዃን ሕዝብ ስላልተወያየበት ተቀባይነተ ሊኖረው አይገባም።" ሲሉ የኦሮሞ ፌዴራሊስ ኮንግረስ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ማምሻውን ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል።