ዶክተር መረራ ጉዲና ወደ ዩናትድ ስቴትስ ጉዟቸዉ ተሰናከለ

Your browser doesn’t support HTML5

የኦሮሞ ፌዴራሲስት ኮንግረስ መሪ ዶክተር መረራ ጉዲና ወደ ዩናትድ ስቴትስ ሊያደርጉ የነበረዉ ጉዟቸዉ ፣ ፓርፖርታቸዉ ላይ ተገኘ በተባለዉ ችግር መሰናከሉን ተናገሩ። ዶክተር መረራ በዚህ ቅዳሜና እሁድ ዋሽንግተን ዲሲ ዉስጥ የሚካሄድ ”Vision Ethiopia” የተባለ ሲቪል ማህበረሰቦችና የፓለቲካ ድርጅቶች ጉባኤ ላይ ንግግር ሊያደርጉ ወዲህ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ሊመጡ ነበር። ፓርፖርታቸ ችግሩ አለዉ መባሉ እስክ ዛሬ መፍትሔ እንዳላገኘ ዶክተር መረሩ ገልጸዋል።