ፕረዚዳንት ኦባማ በኩባው ጉብኝታቸው “የመጨረሻውን የቀዝቃዛው ጦርነት ርዝራዥ” እንደሚቀብሩ አስታወቁ

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ ዛሬ ኩባ ባደረጉት ታሪካዊ ንግግር ሁለቱ ሀገሮች ከባድ የግንኙነት ታሪክ ቢኖራቸውም ለኩባ ህዝብ “የሰላም መልእክት” እንሚደሚያቀርቡ ገልጸዋል። የትላንት ጉብኝታቸው የክብር ስነ-ስርአቶችና ተምሳሌታዊነት የሰፈነበት ነበር። ይሁናን በሁለቱም ሃገሮች መካከል ያለው ልዩነትም መንጸባረቁ አልቀረም።