የካሜሩንና የናይጄሪያ ጦር ኃይሎች የነውጠኛው ቦኮ ሀራም ታጋቾችን ነፃ አወጡ

Your browser doesn’t support HTML5

የካሜሩንና የናይጄሪያ ጦር ኃይሎች፥ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የነውጠኛው ቦኮ ሀራም ታጋቾችን ነፃ አወጡ። ታጋቾቹ ሴቶችና ልጃገረዶች አንድም በግዳጅ እንዲያገቡ የተደረጉ አልያም ለወሲብ ባርነት የተሸጡ ነበሩ ተብሏል። ታጋቾቹ ነፃ የወጡት በካሜሩንና በናይጄሪያ መካከል በምትገኘው አቺጋቻ (Achigachia) ላይ ወረራ ከተካሄደ በኋላ መሆኑም ታውቋል።