ዶክተር ብርሃኑን ወደ ዋሺንግተን ያመጣቸው ጉዳይ ምንድነው?
Your browser doesn’t support HTML5
የአርበኞች ግንቦት 7 የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀ መንበር ዶክተር ብርሃኑ ነጋ ባሁኑ ወቅት እዚህ በዩናይትድ ስቴትስ ይገኛሉ። በቅርቡ በወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ለአውሮፓ ፓርላማ አባላት ማብራሪያ ለመስጠት ብራሰልስ እንደነበሩም ተዘግቧል።