ኬንያ ውስጥ ክርስቲያኖችን ለማዳን ሲል የቆሰለው የእስልምና እምነት ተከታይ አርፏል

Your browser doesn’t support HTML5

የአል-ሸባብ ነውጠኞች ባለፈው ወር ሰሜን ምስራቅ ኬንያ ውስጥ በአንድ አውቶቡስ ላይ ጥቃት ባደረሱበት ወቅት፥ ከክርስቲያን ወንድሞቼ አልለይም በማለቱ በጥይት ተመትቶ የቆሰለው የእስልምና እምነት ተከታይ አርፏል። ግለሰቡ ናይሮቢ በሚገኘው ኬንያታ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ ሲደረግለት ቆይቶ ያረፈው ባለፈው እሁድ መሆኑ ታውቋል። የቪኦኤ ባለደረባችን ጂል ክሬግ (Jill Craig) አጠናቅራዋለች፣ ሰሎሞን ክፍሌ አቀቦታል።