ጂቡቲ ከኢራን ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋርጣለች

  • ሰሎሞን ክፍሌ

Your browser doesn’t support HTML5

ጂቡቲ ቴህራን በሚገኘው የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ከኢራን ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋርጣለች። ጂቡቲ፥ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በዓለምአቀፍ ትብብር ቃል አቀባይዋ በኩል ትላንት ባወጣችው መግለጫ፥ የመንግሥቱ ቃል አቀባይ በቴህራንና  በማሻድ(Mashhad)  የደረሱትን ጥቃቶ በከፍተኛ ደረጃ አውግዟል ብሏል። ኢራን ዓለምአቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ግዴታዎቿን ማክበር ይጠበቅባታል ሲልም መግለጫው አክሏል።