የይግባኝ ሰሚ ችሎት ዳኛ የእነ አቶ ሃብታሙ አያሌው ጉዳይ ከችሎት እንዲነሡላቸው ጠይቁ
Your browser doesn’t support HTML5
በበታች ፍርድ ቤት በነፃ ተሰናብተው የነበሩት እነ አቶ ሃብታሙ አያሌው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ሰብሳቢ ዳኛ ከችሎት እንዲነሡላቸው ጠይቀዋል። አቶ ሃብታሙ በጠና የታመሙ መሆናቸውንና ሃኪሞች ያዘዙላቸውን ሕክምና እንዳያገኙ በማረሚያ ቤቱ መከልከላቸውን አሳውቀዋል።