በአፍጋኒስታን የሚገኘው የዩናትድ ስቴትስ ኤምባሲ ለዜጎቹ ማስጠንቀቅያ ሰጠ

Your browser doesn’t support HTML5

ዩናትድ ስቴትስ (United States) በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ውስጥ በአፍጋኒስታን መዲና “ጥቃት መካሄዱ አይቀርም የሚል አስተማማኝ ዘገባ ስለደረሳት” የአሜሪካ ዜጎች ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ በጥብቅ አሳስባለች። የዩናትድ ስቴትስ (United States) ኤምባሲ ዛሬ ለዜጎቹ የላከው አስቸኳይ መልእክት ስለኢላማዎቹም ሆነ ስለሚካሄድበት ጊዜና ስለጥቃቱ ዘዴ በዝርዝር የተገለጸ ነገር እንደሌለ ጠቁሟል። የአሜሪካ ዜጎች ወደ አፍጋኒስታን እንዳይጓዙም ጨምሮ አስጠንቅቋል።