ቦትስዋና ለ10 የኤርትራ ተጫዋቾች የሰጠችውን የጥገኝነት ፍቃድ አልቀለበሰችም

Your browser doesn’t support HTML5

የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ማጣርያ ግጥሚያ ለመሳተፍ ወደ ቦትስዋና በቅርብ ለሄዱት 10 የኤርትራ ብሔራዊ የእግር ኳስ ተጫዋቾች የፖለቲካ ጥገኝነት የቦትስዋና መንግስት ፈቅዶላቸው እንደነበር ይታወሳል። ስፖርተኞቹ ጥቅምት 2 ቀን 2008 ዓ.ም. ከቦትስዋና ቡድን ጋር ከተጫወቱ በውኃላ ነው ወደ ሃገራቸው በሚወስዳቸው አውሮፕላን ላይ አንሳፈርም በማለት በቦትስዋና ጥገነት የጠየቁት።