የተመስገን ደሣለኝ ጤና /ርዝመት - 13ደ 03ሰ/

Your browser doesn’t support HTML5

የፍትሕና ልዕልና ጋዜጦች፣ እንዲሁም የፋክትና የአዲስ ታይምስ መፅሔቶች ባለቤትና አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሣለኝ ከታሠረ ፤ ጥቅምት 3 ቀን 2008 ዓ.ም አንድ ዓመቱን ደፍኗል፡፡ የተመስገን ጤና አሳሳቢ መሆኑን ቤተሰቡቹ ገልጸዋል፡፡ ማረሚያ ቤቱ ግን ተመስገን ሕክምና እያገኘ መሆኑን ጤናማም እንደሆነ ይናገራል፡፡