ሳምንታዊ የስፖርት ዝግጅት

  • ሰሎሞን ክፍሌ

Your browser doesn’t support HTML5

ቻይና ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ ለአሥር ቀናት የሚቆየውን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ታስተናግዳለች። በዚህ አሥራ አምስተኛው የዓለም ሻምፒዮና ውድድር ላይ ከሚሳተፉ 61 አትሌቶች መካከል የመጀመሪያው ቡድን አባላት ትላንት እሁድ ተሸኝተዋል። ቅዳሜ በመክፈቻው እለት የሚካሄደውን የማራቶን ሩጫ ጨምሮ፥ የኢትዮጵያ አትሌቶች በተለያዩ የመካከለኛና ረዥም ርቀት ውድድሮች የወርቅ ሜዳልያ ሊያገኙ እንደሚችሉ ከወዲሁ እየተነገረ ነው።