አቶ አንዳርጋቸው ከተማ እንደሚጎበኙ ዶ/ር ቴዎድሮስ ተናገሩ

Your browser doesn’t support HTML5

በኢትዮጵያ እስር ቤት የሚገኙት የግንቦት ሰባት ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ በተሻለ ሁኔታ መያዛቸዉን የአገሪቱ ዉጭ ግዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገለጹ። ሚኒስትሩ ትላንት ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዩ የአማርኛዉ ቋንቋ ስርጭት ስለ ፕሬዚደንት ኦባማ ኢትዮጵያ ጉብኚት በሰጡት ቃለ ምልልስ ስለ አቶ አንዳርጋቸዉ አያያዝ ተጠይቀዉ ፣ ታሳሪዉ በመኪና ሆነዉ አገሪቱ በልማት እያደረገች ያለችዉን ግስጋሴ እንዲጎበኙ ሁሉ እንደሚደረግ ተናግረዋል።