ሳምንታዊ የስፖርት ፕሮግራም ግንቦት 3 ቀን 2007 ዓም

በዓለም ዝነኛው አትሌት ኢትዮጵያዊው ኃይሌ ገብረሥላሴ ከእንግዲህ በሩጫው ስፖርት ውድድር እንደማይሰለፍ በይፋ አስታወቀ። ውሳኔው በውድድር መልክ የሚካሄድ ሩጫን እንጂ ”ሕይወቴ” ነው ያለውን መሮጥ ለማቆም እንዳልሆነ ግን አስረድቷል።

ሁለቴ በኦሊምፒክስ ወርቅ ተሸላሚው ኃይሌ ይህን ውሳኔውን ያስታወቀው፥ ከዚህ ቀደም አምስቴ ሻምፒዮን በሆነበት በታላቁ የማንቸስተር ሩጫ ውድድር ፍጻሜ ላይ በ 16ኝነት ካጠናቀቀ በሁዋላ ነው።

ከ 20 ዓመታት በላይ ባስቆጠረው ስኬታማ የሩጫ ውድድር ታሪኩ፥ ኃይሌ 15 የዓለም ክብረ ወሰኖችን አስመዝግቧል። በሁለት ርቀቶች አሁንም የተስተካከለው አትሊት የለም።

Your browser doesn’t support HTML5

Amharic Sport