ዋሺንግተን ዲ.ሲ —
Your browser doesn’t support HTML5
የግንቦት ሰባት የፍትሕ፣ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የመን ውስጥ በመንግሥቱ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
አቶ አንዳርጋቸው የመን ዋና ከተማ ሰንዓ አይሮፕላን ጣቢያ ላይ የተያዙት ባለፈው ሣምንት ሰኔ 16 መሆኑን ግንቦት ሰባት አስታውቋል፡፡
አቶ አንዳርጋቸውን ለማስለቀቅ ባለፈው ሣምንት ውስጥ የእንግሊዝን ኤምባሲ ጨምሮ በርካታ ጥረቶች ቢደረጉም የየመን መንግሥት ግን ለመልቀቅ ፍቃደኛ ሳይሆን መቅረቱንና ድርጅቱ የመሪውን ጉዳይ ወደ ሕዝብ መውሰድ አስፈላጊ ሆኖ ያገኘው መሆኑን የግንቦት ሰባት ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡