ዋሽንግተን ዲሲ —
Daily News የተባለው የግብጽ ጋዜጣ የግብጽ የውሀ ሀብትና የመስኖ ሚኒስትር ስለ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ውይይት እንዲደረግ ላቀረቡት ጥሪ ኢትዮጵያ ምላሽ አለምስጠትዋ ግብጽን አሳስቧል ሲሉ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ Badr Abdel Atty እንደተናገሩ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ የግብጽና የሱዳን የውሀ ሀብት ሚኒስትሮች ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግብጽንና ሱዳንን በመሳሰሉት የግርጌ ተፋሰስ ሃገሮች ላይ ሊኖረው ስለ ሚችለው አንደምታ አለም አቀፍ የጠበብት ኮሚቴ ያቀረበው ዘገባ መተግበርን በሚመለከት በቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር አቅደዋል።
ግብጽ ንግግሩ እንዲካሄድ በድጋሚ ጥሪ እንደምታደርግ አንድ የግብጽ ዲፕሎማስያዊ ምንጭ ጠቁሟል ይላል የግብጹ ጋዜጣ።
በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር ማሕሙድ ድሪር በበኩላቸው እሚያሳስብ ነገር የለም። ስብሰባው ይካሄዳል። ኮሚቴው ያቀረባቸው ሃስቦችም ይመክሩባቸዋል ማለታቸውን ሽንዋ የተባለው የቻይና የዜና አገልግሎት ዘግቧል።
ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር ያላትን ጠንቃራ ግንኙነት የመጠበቅ ጽኑ ፍላጎት አላት። በአባይ ወንዝ ላይ የሚገነባው ታላቁ ህዳሴ ግድብም በሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት የውጥረት ምንጭ አይሆንም። የህዳሴ ግድብ መገንባት የግብጽን የውሀ ድርሻ አይጎዳም። የሚጠቀሙትም ሁለቱ ሀገሮች ናቸው ሲሉ አምባሳደሩ እንዳስገነዘቡ ሽንዋ ዘግቧል።

Your browser doesn’t support HTML5