የኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ጉባዔ በዋሺንግተን ዲ ሲ ተጠራ

  • ሰሎሞን ክፍሌ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት፥ «ሁሉን አቀፍ» ሲል የጠራውን ጉባዔ በቅርቡ እዚህ ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ እንደሚያካሂድ ገልጿል። በዚህ ከፖለቲካ ድርጅቶች እስከ ውጭ ሀገር እንግዶች ይሳተፉበታል የተባለው ጉባዔ ምን ምን ምን አጀንዳዎች ይዳስሳሉ ? ከቀደምቱ ተመሳሳይ ጉባዔዎችስ በምን ይለያል ?

ሰሎሞን ክፍሌ የምክር ቤቱን ዋና ጸሐፊ ዶክተር ፍስሃ እሸቱን አነጋግሯል። ዓላማውን በማስረዳት ይጀምራሉ።

Your browser doesn’t support HTML5

ሙሉ ውይይቱን ከዚህ ያድምጡ