ዋሺንግተን ዲሲ —
የኢትዮጵያ አትሌቶች በሳምንቱ ማብቂያ በተለያዩ የዓለም ከተሞች በተካሄዱ ዓለምአቀፍ የሩጫ ውድድሮች ድል ተቀዳጅተዋል። በ 37ኛው የፓሪስ ማራቶን በሴቶቹ የሥፍራውን አዲስ ክብረወሰን አስመዝግባ ያሸነፈችው ፈይሴ ታደሰ ናት። መሪማ መሃመድ ሁለተኛ ሆናለች።
በካሊፎርኒያው ካርልስባድ 5 ሺህ ሜትር በሁለቱም ጾታዎች ያሸነፉትም የኢትዮጵያ አትሌቶች ናቸው። በወንዶቹ ደጀን ገብረመስቀል፥ በሴቶቹ ደግሞ ገለቴ ቡርቃ ቀድመው ገብተዋል።
በእግር ኳስ፥ ቅዱስ ጊዮርጊስና ደደቢት የአፍሪቃ ክለቦች ሻምፒየንስ ሊግና የአፍሪቃ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የመልስ ማጣሪያቸውን ትላንት እሁድ በአዲስ አበባና በባማኮ አከናወኑ። ጊዮርጊስ ወደቀጣይ ዙር አለፈ፥ ደደቢት ወጣ።
Your browser doesn’t support HTML5