ኢትዮጵያ በጋዜጦች

Ukrayna hərbiçisi və həkim yaralı əsgəri Slavyanskın yaxınlığındakı İzyum xəstəxanasına aparır - 3 iyun, 2014

Ukrayna hərbiçisi və həkim yaralı əsgəri Slavyanskın yaxınlığındakı İzyum xəstəxanasına aparır - 3 iyun, 2014

theguardian የተባለው የብሪታንያ ጋዜጣ ድረ-ገጽ በዘገበው መሰረት በኦጋደን ክልል በርካታ የሰብአዊ መብት ረገጣዎችና ግድያዎች ፈጽመዋል በሚል የሚከሰሱትን ልዩ የጸጥታ ሀይሎችን ለማሰልጠን ብሪታንያ በሚልዮኖች የሚቆጠር ፓውንድ ታወጣለች።

የብሪታንያ የአለም አቀፍ ልማት ክፍል የውስጥ ሰነድን እንደተመለከተ የገልጸው ድረ-ገጽ በሶማሊ ክልል በሚገኘው ኦጋደን ያሉት የጸጥታ ሀይሎችን የማሰልጠኑ እቅድ በክልሉ ለማካሄድ በታቀደው የአምስት አመታት የሰላም እቅድ መሰረት ሲሆን ከ 13 እስከ 15 ሚልዮን ፓውንድ ወጪ እንደሚደረግ ድረ-ገጹ ጠቁሟል።

የብሪታንያው የአለም አቀፍ ልማት ክፍል የአከባቢው የጸጥታ ሁኔታ እንዲሻሻልና የጸጥታ ሀይሎቹ ተጠያቂነትና ሙያዊ አሰራር እንዲኖራቸው ለማሰልጠን የተደረገውን እቅድ የሚያንቀሳቅሱት መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የግል ኩባንያዎች ናቸው ማለቱን ጽረ-ግጹ አውስቷል።

በሌላ ዜና ደግሞ ኢትዮጵያን ከጎረቤት ሀገር ሱዳን ጋር የሚያገናኘው አውራ ጎዳና ግንባታ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት እንደሆነ የኢትዮጵያ የመንገድና የመጓጓዣ ባለስልጣን ባለፈው ማክሰኞ እንዳስታወቀ የሚገልጽ ዘገባ አለን።

Your browser doesn’t support HTML5

AMH-af-Ethiopia-Press-Review-1-18-13