ኢትዮጵያ በጋዜጦች

Ethiopian Refugees in Yemen

ወደ ሳውዲ አረብያ ለመሄድ ተጉዘው በሃራድ ከተማ መውጫ አጥተው ከቆዩ በኋላ በየመን ድንበር ሀራድ ከተማ ለብዙ ወራት መውጫ አጥተው ሲሰቃዩ ቆይተው ባለፈው ረቡእ በፍላጎታቸው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል ሲል የመን ታይምስ ድረ ገጽ ዘግቧል። 216 ኢትዮጵያውያን IOM ማለት አለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት ወደ ሃገራቸው ለመመለስ እንዲረዳቸው ጠይቀው እንደተባበራቸው የመን ታይምስ ጠቅሷል።

አፍሪቃ ነክ የሆኑ ዜናዊችን በማቅረብ ረገድ አንጋፋ የሆነው Africa Press Organization ማለት የአፍሪቃ የፕረስ ድርጅት ደግሞ ስደተኞቹ IOM ባዘጋጀላቸው የቻርተር አይሮፕላን በረራ እንደተመለሱ ገልጿል።

የመጓጓዣው ገንዘብ የተገኘው ኒዘርላንድስ ከሰጠችው 2.1 ሚልዮን ዶላር ሲሆን ከአቻ አምና አንስቶ 9,500 የሚሆኑ በድህነት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከየመን እንዲወጡ አድርጓል ሲል የፕረስ ድርጅቱ ጠቁሟል።

MLT የተባለው በየእለቱ የሚወጡ ህክምና ነክ ዜናዎችን የሚያሰራጨው ድረ-
ገጽ ደግሞ በኢትዮጵያና በቲቤት የሚኖሩ ደገኞች የኦክሲጅን እጠረት ባለበት፣ ከፈታማ ቦታ ለምኖር የሚያስችላቸው ስነፍጥረታዊ ብቃት አላቸው ይላል።

እንድታደምጡ እንጋብዛለን።

Your browser doesn’t support HTML5

AMH-af-Ethiopia-Press-Review-12-14-12