«ልበ ብርሃኑ፥» ጋዜጠኛ

ዶ/ር መሠረት ቸኮል

ጥልቀት ባላቸው ትንታኔዎቹና ቀላል አቀራረቡ የሚታቀው ጋዜጠኛና መምህር በተለይ ለኢትዮጵያ አድማጮች “ጠቀሜታ ይኖራቸዋል፤” ባላቸው ርእሰ ጉዳዮች፥ ውጥኖችና ገቢሮች ዙሪያ በትጋትና በኃላፊነት ለረዥም ጊዜ ያለ መታከት ያበረከተው አስተዋጽኦ ጎልቶ የሚነገርለት ነው።

የመገናኛ ብዙኃንና ጋዜጠኝነትን የሚመለከቱ ፕሮግራሞችና የዩናይትድ ስቴትስ ፖለቲካ የውይይት ርዕስ ሆኖ በሚቀርብባቸው ዝግጅቶች የሚዛናዊ ባለ ሞያ ድምጽ በመሆን ለረዥም ዓመታት በንቃት ተሳትፏል።
ያ ድምጽ ዛሬ ግን ከእኛ ጋር የለም።

ዶ/ር መሠረት ቸኮል፥ በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ በዊስኮንሰን ክፍለ ግዛት ሪቨር ፎልስ በጋዜጠኝነት ሞያና የመገናኛ ብዙኃን መምህርነት አገልግሏል።
ለመሆኑ ዶ/ር መሠረት ማን ነው? ምን ዓይነት ሠው ነበር?

ልጅነት፥ የቀድሞው መርሃ እውራን ተማሪ ቤትና ኮሌጅ? ሞያና ህይወት በተከታታዩ ቅንብሮች ተካተዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

(1) የኢትዮጵያውያን የህይወት ታሪክ መረጃ ማዕከል


(2) ተማሪ ቤትና ጋዜጠኝነት፤ ሞያና ህይወት

Your browser doesn’t support HTML5

2-1 ቆይታ ከአቶ ሙልጌታ ሉሌ ጋር


Your browser doesn’t support HTML5

2-2 ቆይታ ከአቶ ማእረጉ በዛብህ ጋር


Your browser doesn’t support HTML5

(3) መንገድ መሪ፤ መልካም አረዓያነት


Your browser doesn’t support HTML5

(4) ልጅነት፥ ጓደኝነት እና የነገ ህልሞች


Your browser doesn’t support HTML5

(5) ቤተሰብ