የፕሬዝዳንት ኦባማ 2ተኛ ዙር የአስተዳደር ዘመንና አገሪቱ የገጠሟት ፈተናዎች

ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ

ኦባማ ለሁለተኛ ዙር አገራቸውን በፕሬዝዳንትነት ለማስተዳደር ያስቻላቸውን ምርጫ ባሸነፉ ማግስት ከፊታቸው የተደቀኑ ፈተናዎች ለመፍታት የሚያስችሉ አቅጣጫዎች መመርመር ይዘዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አብላጫ መቀመጫዎችን ከያዘው ከተፎካካሪው የሪፐብሊካን ፓርቲ አባላት ጋር አብሮ ለመሥራት የሚያስችሉ አማራጮችን ለማጤን የሁለቱ ወገን ንግግርም ጀምሯል።

ለመሆኑ ቀጣዩ የሁለተኛ ዙር የአስተዳደር ዘመናቸው ምን ዓይነት ገጽታ ይኖረው ይሆን? የዛሬው የትንታኔ ውይይት ይበልጡን በኦባማ አስተዳደር የውጭ ፖሊሲ አቅጣጫ፥ ፈተናና አማራጮች ላይ ያተኩራል።

ሞያዊ ትንታኔውን የሚሰጡን፥ ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማሪያም የካሊፎርኒያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህርና የኅግ ባለ ሞያ እና ፕሮፌሰር ጌታቸው መታፈሪያ በሞርጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ናቸው።

Your browser doesn’t support HTML5

የፕሬዝዳንት ኦባማ 2ተኛ ዙር የአስተዳደር ዘመን ገጽታ፤ የውይይቱን የመጀመሪያ ክፍል ከዚህ ያድምጡ


Your browser doesn’t support HTML5

ሁለተኛውን ክፍል ከዚህ ያድምጡ