በኦባማ መመረጥ ላይ ያላቸዉን ጉጉት መቀነሱን ኢትዮጵያዉያን አስተያየት ሰጪዎች ተናገሩ

  • እስክንድር ፍሬው

በአሜሪካ የመንግስት ለዉጥ በኢትዮጽያ ያለው ተጽኖ

በልእለ ሀያልዋ ሀገር አሜሪካ የሚካሄዱ ፕሬዚደንታዊ ምርጫዎች ከዚህች አገር አልፈዉ የሌሎችንም አገሮች ትኩረት መሳባቸዉ የተለመደ ነዉ።

በኢትዮጵያም ቢሆን ሁኔታዉ ተመሳሳይ ሆኖ ቆይቷል። በተለይ የዛሬ አራት ዓመት በአፍሪቃ አሜሪካዊዉ ባራክ ኦባማና በሬፑብሊካን ፓርቲ እጩ ሴናተር ጆን ማኬይን መካከል የተካሄደዉ ፉክክር የተለየ ትርጉም ጭምር ነበረዉ።

በየሃገሮቻቸዉ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ያለመኖሩን ያመኑ የአፍሪቃ አገሮች ዜጎች በተለይ ከመጀመሪያዉ ጥቁር የአሜሪካ ፕሬዚደንት የጠበቁት ተጽእኖ በተለያዩ ሁኔታዎች ተንጸባርቀዋል። ዛሬ ከአራት ዓመታት በሁዋላ እኚሁ ጥቁር ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ ከሌላዉ የሬፑብሊካን ፓርቲ እጩ ሚት ሮምኒ ጋር ለዳግም ምርጫ ተፋጠዋል።

የሆነ ሆኖ አንዳንድ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ”በአሜሪካ ዉስጥ የሚደረግ የመንግስት ለዉጥ ለኢትዮጽያ የሚያስገኘዉ ፋይዳ እንደሌለዉ በባራክ ኦባማ አራት የፕሬዚደንትነት ዓመታት ተገንዝበናል” ሲሉ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል።

Your browser doesn’t support HTML5

ዝርዝሩን አስተያየቶችን ካሰባሰበዉ እስክንድር ፍሬዉ ዘገባ ያድምጡ