በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በገላና ወረዳ በቀጠለው ውጊያ የጤና እና የትምህርት አገልግሎቶች ተቋርጠዋል


የኢትዮጵያ ካርታ
የኢትዮጵያ ካርታ

በድጋሚ የታደሰ

ካለፉት ሳምንታት አንሥቶ፣ በምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ በርካታ አካባቢዎች፣ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እና በመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች መካከል እንደቀጠለ በተገለጸው ውጊያ፣ በአካባቢው የጤና እና ትምህርት ተቋማት መቋረጣቸው ተነግሯል።

የገላና ወረዳ ጤና ቢሮ ኃላፊ፣ ከወረዳው ከተማ ውጭ ያሉ የጤና ተቋማት የተሟላ አገልግሎት እየሰጡ እንዳልኾነና በርካታ የጤና ኬላዎች ኦነግ ሸኔ ባሉት አካል እንደተቃጠሉ ገልጸዋል።

የገላና ወረዳ ጸጥታ እና ደኅንነት ጽ/ቤት፣ ወረዳውን ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አማሮ ዞን የሚያገናኘው የአምስት ኪሎ ሜትር መንገድ፣ “ታጣቂዎች በሕዝብ ላይ ጥቃት እንዳያደርሱ” በሚል ለተሽከርካሪ ዝግ መደረጉን አመልክተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

 በገላና ወረዳ በቀጠለው ውጊያ የጤና እና የትምህርት አገልግሎቶች ተቋርጠዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:15 0:00

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG