በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ቲክቶክን ሊያግድ የሚችል ህግ አፀደቀች


ቲክቶክ
ቲክቶክ

የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክርቤት፣ የቲክቶክ እናት ኩባንያ የሆነው ባይት ዳንስ ድርጅት የቪዲዮ ማጋሪያውን አውታር ለአሜሪካ እንዲሸጥ ወይም በአገሪቱ የመታገድ እጣ ፈንታ እንዲጋፈጥ የሚጠይቅ ህግ አጽድቋል።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ረቂቅ ህጉን ረቡዕ በፊርማቸው አፅድቀዋል። ባይት ዳንስ ቲክቶክን በአንድ ዓመት ውስጥ ለመሸጥ ፈቃደኛ ካልሆነ በአሜሪካ ተጠቃሚዎች ዘንድ ይታገዳል።

ቲክቶክ እንዲታገት የሚሟገቱ ሰዎች ባይትዳንስ ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ጋር የመተባበር ታሪክ እንዳለው እና መተግበሪያው የአሜሪካን ተጠቃሚዎች መረጃ ለቻይና መንግስት ያቀብላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ይገልጻሉ።

ቲክቶክ በበኩሉ በተጠቃሚዎች መረጃ እና በማናቸውም የውጭ ጣልቃገብ በሆኑ አጠቃቀሞች መካከል የደህንነት ግድግዳ ያቆመ መሆኑን በመጥቀስ እኒህን ክሶች ሲቃወም ቆይቷል።

እገዳው ሰባት ሚሊየን ንግዶችን እንደሚያጠፋ እና ከ170 ሚሊየን በላይ አሜሪካውያንን እንደሚያፍን"

የቲክቶክ ፖሊሲውን በሚተነትንበት የኤክስ መተግበሪያ ላይ ባስተላለፍው መልዕክት "እገዳው ሰባት ሚሊየን ንግዶችን እንደሚያጠፋ እና ከ170 ሚሊየን በላይ አሜሪካውያንን እንደሚያፍን" ገልጿል። እውነታው የአሜሪካ መረጃ ደህንነት የተጠበቀ እና መተግበሪያችንም ከውጪ ተፅእኖ እና ከማንኛውም ማጭበርበር ውጪ እንዲሆን በቢሊየኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን ወጪ ማድረጉ መሆኑን በመግለፅም፣ የዩናይትድ ስቴትስን ውሳኔ ተቃውሟል።

የቲክቶክ መልዕክት አክሎ "ይህንን ኢ-ህገመንግስታዊ እገዳ እየተቃወምን ባለንበት ወቅት ቲክ ቶክ ለአሜሪካውያን ደህንነታቸው የተጠበቀ ስፍራ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚያስችለንን ፈጠራ እና መዋዕለ ንዋይ ማፍሰሳችንን እንቀጥላለን" ብሏል።

ቲክቶክ 170 ሚሊየን የአሜሪካ ተጠቃሚዎች ለሕግ አውጪዎቻቸው እንዲደውሉ በማበረታታት እና ለቴሌቭዥን ማስታወቂያዎች 5 ሚሊየን ዶላር በማውጣት ፖለቲካዊ ጥቃት መጀመሩን፣ ማስታወቂያዎችን የሚከታተለው አድ-ኢምፓክት የተሰኘው ድርጅት መረጃ ያመለክታል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG