በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲሱ የቲክቶክ መተግበሪያ በአውሮፓ ኮሚሽን ጥያቄ ቀረበበት


የቲክቶክ አርማ
የቲክቶክ አርማ

አዲሱ መተግበሪያው “ቲክቶክ ላይት” በፈረንሳይ እና ስፔይን አገልግሎት የጀመረው ቲክቶክ በህጻናት እና ተጠቃሚዎች የአዕምሮ ጤንነት ላይ ሊያስከትል ስለሚችለው አደጋ ያለውን ግምገማ በ24 ሰዐት ውስጥ እንዲያቀርብ ዛሬ ረቡዕ የአውሮፓ ኮሚሽን ጠየቀ።

ከዋናው ቲክቶክ መተግበሪያ አነስ ብሎ የወጣው የቲክቶክ መተገበሪያ ተጠቃሚዎች ተከፍሏቸው የቪዲዮ ምስሎችን እንዲመለከቱ በማድረግ በሚያስቆጥሯቸው ነጥቦች የመግዛት አቅምና ዋጋ ያላቸውን የስጦታ ካርዶችን የሚሽልም ነው፡፡

በመተግበሪያው ተሳታፊ ለመሆን ተጠቃሚዎች ቢያንስ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

ሽልማቱን ለማግኘት በቀን እስከ 1.06 ዶላር የሚደርስ ሽልማት ለማግኘት በየቀኑ አንድ ሰዐት ድረስ ቪዲዮውን መመልከት ይችላሉ፡፡

የአእውሮፓ ኮሚሽን የቻይናው የቲክ ቶክ ባለቤት ባይትዳንስ (ByteDance) መተግበሪያውን ከመልቀቁ በፊት ሊያስከትል ስለሚችለው አደጋ ቁጥጥርና ጥንቃቄ ግምገማ ማድረግ ነበረበት ብሏል።

አዲሱን መተግበሪያ  በተመለከተ ከኮሚሽኑ ጋር በቀጥታ ተገናኝተናል፣ ለቀረበልን ጥያቄም ምላሽ እንሰጣለን”

ጥያቄው የቀረበው ቲክቶክ ያወጣው አዲሱ “Task and Reward Lite” የተባለው መተግበሪያ፣ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ሕፃናትን ደህንነት እንዲሁም በተጠቃሚዎች የአእምሮ ጤና ላይ ፣ በተለይም ሱስ አስያዥ ባህሪን ከማነሳሳት ጋር ተያይዞ ሊያመጣ የሚችለውን ተፅእኖ መሰረት በማድረግ ነው” ሲል የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡።

ጥያቄው የቀረበው ቲክ ቲኮን ጨምሮ ወደ 22 በሚደርሱ ዋና ዋና የኢንተርኔት መተግበሪያ መድረኮች ላይ የሚወጡ ይዘቶችን ለመቆጣጠር እኤአ በ2022 በወጣው የዲጂታል አገልግሎቶች ህግ መሰረት ነው፡፡

ሊያስከትል ስለሚችለው አደጋ ቁጥጥርና ጥንቃቄ ያለውን ግምገማ እንዲያቀርብ ከተሰጠው የ24-ሰዐት የጊዜ ገደብ ባሻገር፣ ቲክ ቶክ የተጠየቀውን ተጨማሪ መረጃ እ ኤ አ እስከ ሚያዝያ 26 ድረስ መስጠት አለበት ሲል ኮሚሽኑ አሳስቧል።

የቲክ ቶክ ቃል አቀባይ “አዲሱን መተግበሪያ በተመለከተ ከኮሚሽኑ ጋር በቀጥታ ተገናኝተናል፣ ለቀረበልን ጥያቄም ምላሽ እንሰጣለን” ማለታቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG