በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አለም አቀፍ የወንጀል ችሎት በኬንያው ምክትል ፕረዚዳንት ላይ ተመስርቶ የነበረውን ክስ ሰርዟል

ፋይል - የኬንያ ምክትል ፕረዚዳንት ዊልያም ሩቶ እ.አ.አ. 2013
ፋይል - የኬንያ ምክትል ፕረዚዳንት ዊልያም ሩቶ እ.አ.አ. 2013

ችሎቱ ዛሬ በተናገረው መሰረት ዳኞቹ በሩቶና አብረዋቸው በተከሰሱት ጃሹዋ አራፕ ሳንግ ላይ ተመስርቶ የነበረው ክስ እንዲሰረዝ 2 በአንድ ድምጽ ወስነዋል።

አለም አቀፍ የወንጀል ችሎት በኬንያው ምክትል ፕረዚዳንት ዊልያም ሩቶ ላይ ተመስርቶ የነበረውን በስብእን ላይ ወንጀል የመፈጽም ክስ ሰርዟል።

ችሎቱ ዛሬ በተናገረው መሰረት ዳኞቹ በሩቶና አብረዋቸው በተከሰሱት ጃሹዋ አራፕ ሳንግ ላይ ተመስርቶ የነበረው ክስ እንዲሰረዝ 2 በአንድ ድምጽ ወስነዋል።

ፋይል ፎቶ - ጃሹዋ አራፕ ሳንግ
ፋይል ፎቶ - ጃሹዋ አራፕ ሳንግ

ሩቶ እ.አ.አ. በ 2007 እና በ 2008 ዓ. ም. ኬንያ ላይ በተካሄደው የድህረ-ምርጫ ግጭት ለተፈጸሙት ግድያዎች፣ ህዝብን በግዴታ ማፈናቀልና ወከባዎች ተጠያቂ ናቸው በሚል ነበር የተከሰሱት። የሀገሪቱ ሬድዮ ስርጭት ሃላፊ ሳንግም በወንጀሉ ሚና ተጫውተዋል በሚል ነበር ክስ የተመሰረተባቸው። በግጭቱ ወቅት 1,100 የሚሆኑ ዜጎች እንዳለቁ ይገመታል።

የኬንያው ፕረዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ግጭቱን በማስታባበር ተግባር በመርዳት በስብእና ላይ ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በአምስት ወንጀሎች ተከሰው እንደነበር የሚታወቅ ነው። ፕረዚዳንቱን ለፍርድ ለማቅረብ የሚያስችል በቂ ማስረጃ አልተገኘም በሚል ባለፈው አመት ግንቦት ወር ላይ ክሱ ተሰርዟል።

XS
SM
MD
LG