በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ አፍሪካ ገዢ ፓርቲ የዙማ መንግሥት የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት(ICC)አባልነቱን እንዲያቋርጥ ጠየቀ


የጃኮብ ዙማ መንግሥት የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት (ICC) አባልነቱን እንዲያቋርጥ ከአገሪቱ ገዢ ፓርቲ አፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ANC) ጥሪ እደቀረበለት የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ኤድና ሞሌዋ ተናገሩ፡፡

የጃኮብ ዙማ መንግሥት የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት (ICC) አባልነቱን እንዲያቋርጥ ከአገሪቱ ገዢ ፓርቲ አፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ANC) ጥሪ እደቀረበለት የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ኤድና ሞሌዋ ተናገሩ፡፡

የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ከዓመታት በፊት በዘር ማጥፋትና በሰብዓዊ ዘር ላይ ወንጀል መፈጸም፤በዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት ለቀረበባቸው ክስ የእስር መያዣ ተቆርጦባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡ በዚህም መሠረት ባለፈው ሰኔ ወር በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ በ25ኛው የአፍሪካ ሕብረት መሪዎች ጉባኤ ለመሳተፍ በተገኙበት ወቅት የደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች እስሩ ተፈጻሚ እንዲሆን ቢወስኑም አልበሽርን በቁጥጥር ስር ለማድረግ ሳይቻል ቀርቷል፡፡ በወቅቱ አልበሽር ስብሰባቸውን አጠናቀው በሰላም ወደ አገራቸው ተመልሰዋል፡፡ የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት (ICC) እና ደቡብ አፍሪካም ከዚህ ጊዜ በኋላ አንገት ለአንገት ተናንቀዋል፡፡

የዓለም አቀፍ ወንጀል ፍርድ ቤት ምልክት(ICC)

የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ (ANC) ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ ሞሌዋ ስለዚህ ሁኔታ ሲናገሩም፤ ባለፈው ሰኔ ወር ለተከሰትው ለዚህ ጉዳይ አልበሽርን ለምን በቁጥጥር ስር እንዳላዋለች ደቡብ አፍሪካ ማብራሪያ እንድትሰጥ ባለፈው ሳምንት ከዓለም አቀፍ ወንጀም ፍርድ ቤት (ICC) ተጠይቃለች፡፡እናም ፓርቲያቸው ፍርድ ቤቱ ለሌሎች ሀገራት በሚሠራበት እኩል እየሠራ ባለመኾኑ ደቡብ አፍሪካም አባልነቷን እንድታቋርጥ በመወሰን ከአፍሪካ ሕብረት ለመቆም መወሰኑን በመግለጽ ያስረዳሉ፡፡

"በአፍሪካ ሕብረት ውስጥ የዓለም አቀፍ ወንጀም ፍርድ ቤት (ICC)ን በተመለከተ ያለማቋረጥ ግምገማ ሲደረግ እንደነበር ይታወቃል፡፡ፓርቲያችን አፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ አሁን አፍሪካ ሕብረት በአይሲሲ ላይ ምንድ ነው የወሰነው ብለን ገምግመን ደቡብ አፍሪካ ከአይሲሲ ጋር ያላት ግንኙነት እንዴት ነው ብለን ፈትሸን፡፡ በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ በእውነቱ ፍርድ ቤቱ ለአፍሪካ ሀገራት የሚሰጠው ግልጋሎት ሌላውን አገራት በሚያገለግልበት እኩሌታ አይደለም ብለን አምነናል፡፡"

ሞሌዋ አያይዘው ሲናገሩ፤ የእስር ማዘዣው የተቆረጠባቸው የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ለምን በቁጥጥር ስር እንደዋሉ አይሲሲ ማብራሪያ ከመጠየቁም አስቀድሞ ፓርቲያቸው ጉዳን ጊዜ ወስዶ ሲያስብበት እንደነበረ ነው፡፡

የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር

"በጉዳዩ ላይ አፍሪካ ሕብረት ውሳኔ ካሳለፈበት ከዛሬ ሁለት ዓመት ጀምሮ ፓርቲያችን እየተከታተለ ነበር፡፡በቃ ይኸው ነው የኾነው አሁን ተግባራዊ ማድረጊያ ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡"

ሞሌዋ ጨምረው ሲናገሩ ፓርቲያቸው አሁንም ቢሆን የዘር ማጥፋትን እና በሰብአቢ ፍጡራን ላይ የሚፈጸም ወንጀልን ለማስቀረት በሚል አይሲሲ የተቋቋመበት መርህ ላይ ትልቅ እምነት እንዳላቸው ተናግረው ከዚህ በኋላ ግን እንዲህ ያሉ እንዲህ ያሉ የዘር ማጥፋትና የሰብዓዊ መብት ወንጀል ጉዳዮች ይህንኑ ጉዳይ ለመዳኘት በተቋቋመው አፍሪካ ፍርድ ቤት መታየት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

"እንደ ደቡብ አፍሪካ መንንግሥት ከአይሲሲ ጋር ያለውን ግንኙነት ስንገመግመው በአፍሪካ ሕብረት ሥር በአፍሪካ አሕጉር የሰብዓዊ መብትን ጥሰትን ለማስቀረትና ተያያዥ ጉዳዮችን ለመዳኘት ከተጀመረው ፍርድ ቤት አሠራር ጋር ያልተያያዘ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህን ጉዳዮች ለማየት ከዚህ ፍርድ ቤት ጋር አብረን ለመስራት ከወዲሁ መጀመር አለብን"

ሞሌዋ አያይዘውም ራሳቸው የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤቱ አባል ሳይኾኑ ሌሎች አገራት አባል እንዲኾኑ የሚያስገድዱ ኃያላን አገራት እንዲሁም በአይሲሲ ላይ የሚያሳርፉት ያልተገደበ ስልጣን ጉዳይ ፓርቲያቸው ጨምሮ እንደሚስስበው ይገልጻሉ፡፡

"እንደሚታወሰው እነዚህ ኃያላን መንግሥታት እራሳቸው የዚህ ፍርድ ቤት አባል አገራት አይደሉም ግን ደግሞ ሌሎች አገራት የአባልነት ፊርማ እንዲፈርሙ ግፊት ያደርጋሉ፡፡ እኛ እንደ ደቡብ አፍሪካ የራሳችንን ውሳኔ ማሳለፍ እንችላለን፡፡ ስለዚህ ይህ ውሳኔም መከበር አለበት ብለን እናምናለን"

ሞሌዋ አክለውም፤ የሱዳኑ ፕሬዝዳንት አልበሽር ባለፈው ሰኔ ወር ለአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ደቡብ አፍሪካ በተገኙበት ወቅት በቁጥጥር ስር ያልዋሉት፤እንደ አፍሪካ አገር መሪነታቸው በአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ላይ ሲገኙ ያለመከሰስ መብት ስላላቸው እንደኾነ ተናግረዋል፡፡

የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ ጀምስ በቲ ሞሌዋን በጉዳዩ ላይ አነጋግሯል ባልደረባችን ጽዮን ግርማ እንደሚከተለው አጠናቅራዋለች፡፡ የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG