በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታየ ደንደአን ጉዳይ እያጣራ መሆኑን ኢሰመኮ ገለፀ


የታየ ደንደአን ጉዳይ እያጣራ መሆኑን ኢሰመኮ ገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:11 0:00

የታየ ደንደአን ጉዳይ እያጣራ መሆኑን ኢሰመኮ ገለፀ

የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ደ’ኤታ አቶ ታየ ደንደአ ቤተሰቦች የቀረበለትን የመብት ጥሰት አቤቱታ እያጣራ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አመልክቷል።

ከታሰሩ ሁለት ሣምንት ያለፋቸውን የአቶ ታየ ደንደአን ባለቤትና የቤተሰቦቻቸውን አቤቱታዎች እየተከታተሉ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የክልሎች የክትትልና ምርመራ ዘርፍ ኃላፊ ሰላማዊት ግርማ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

የአቶ ታየ ቤተሰብ አባላት “ከመንግሥት ቤት እንድንወጣ የተደረነው ያለአግባብ ነው” ማለታቸውንና ቤተሰቡ ይጠቀምበት የነበረው የባንክ ሒሳብ መዘጋቱ ጨምሮ የቀረቡለትን አቤቱታዎች ኮሚሽኑ እየተከታተለ መሆኑንና በተመለከተ ጭምር የሚደርስበትን በቅርቡ እንደሚያሳውቅ ወ/ሮ ሰላማዊት አመልክተዋል።

የባለቤታቸው የባንክ ሒሳብ በመዘጋቱ ቤተሰባቸው ለችግር መጋለጡን የአቶ ታዬ ደንደአ ባለቤት ወ/ሮ ስንታየሁ አለማየሁ ተናግረዋል። እርሣቸው እንደማይሠሩና ቤተሰባቸውን እየደገፉ ያሉት በሰው እርዳታ እንደሆነ ገልፀዋል።

“በሰላም ችግር ምክንያት ከየቦታው ተፈናቅለው እኛ ጋር ተጠልለው ያሉ የቤተሰብ አባላትም በስጋት ውስጥ ናቸው” ብለዋል ወ/ሮ ስንታየሁ።

“በቀን አንዴ እየሄድን እንጎበኘዋለን። ልጆቹን ወስጄ ላሳየው ግን አልቻልኩም። የሚፈቀድልን ሦስት ደቂቃ ብቻ ነው። የክስ መዝገብ አልተከፈተበትም። ከጠበቃ ጋርም አልተገናኘም” ብለዋል።

ተዘጉ የተባሉ የባንክ ሒሳቦችና በቤተሰቡ የቀረቡ ሌሎች አቤቱታዎችን በተመለከተ ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ምላሽ ለማግኘት የእጅ ስልካቸው ላይ ጭምር በመደወል ያደረግነው ጥረት አልተሳካም ።

ከመስከረም 2014 ዓ.ም. በቁጥጥር እስከዋሉበት ታህሳስ 2016 ዓ.ም. ድረስ የሰላም ሚኒስትር ደ’ኤታ ሆነው ያገለገሉት አቶ ታየ ደንደአ የኦሮሚያ ክልል ጨፌ ወይም ምክር ቤት አባል ናቸው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG