በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የታየ ደንዳኣ እስር የጠቅላይ ሚኒስትሩን “የውስጥ ተቃውሞ ስጋት ይጠቁማል” ተባለ


የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል አመራር ዶክተር ሚልኬሳ ሚዳጋ፣ የሕግ ባለሞያ አቶ ዳንኤል ውብሸት
የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል አመራር ዶክተር ሚልኬሳ ሚዳጋ፣ የሕግ ባለሞያ አቶ ዳንኤል ውብሸት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ደ’ኤታ አቶ ታየ ደንዳኣን ከሥልጣን በማንሣት ለእስር መዳረጋቸው፣ “በፓርቲውም ኾነ በመንግሥታቸው ውስጥ የሚነሣን ተቃውሞ እንደሚሰጉ ያሳያል፤” ሲሉ፣ ነዋሪነታቸውን በአሜሪካ ያደረጉት የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል አመራር ዶክተር ሚልኬሳ ሚዳጋ ተናገሩ፡፡

ለአገሪቱ የሰላም ዕጦት መንግሥትን ተጠያቂ ያደረጉት አቶ ታየ፣ ጦርነት እንዲቆምና ዕርቅ እንዲደረግ በመናገራቸው ከሥልጣናቸው እንደተነሡ፣ ከእስሩ አስቀድመው ገልጸዋል፡፡ የፌደራል የጸጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኀይል ግን፣ መንግሥትን ለመጣል ከሽብር ቡድኖች ጋራ በኅቡእ ያሴራሉ፤ በማለት በቁጥጥር ሥር እንዳዋላቸው ይፋ አድርጓል፡፡

የሕግ ባለሞያ የኾኑት አቶ ዳንኤል ውብሸት ደግሞ፣ ለእስሩ የቀረቡ መንግሥታዊ ክሶች፣ “አሳማኝ ያልኾኑና ሒደቱም የሕዝብ ተመራጩን ያለመከሰስ መብት የጣሰ ነው፤” ሲሉ ይተቻሉ፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

የታየ ደንዳኣ እስር የጠቅላይ ሚኒስትሩን “የውስጥ ተቃውሞ ስጋት ይጠቁማል” ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:23 0:00

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG