በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን እንድትፈታ ሲፒጄ ጠየቀ


ሲፒጄ
ሲፒጄ

የኢትዮጵያ መንግሥት በመገናኛ ብዙኃን ላይ የሚያካሂደውን ማዋከብ እያባሰ መሄዱን የጠቀሰው ዓለምአቀፍ የጋዜጠኞች ደህንነት ተሟጋች ቡድን /ሲፒጄ/ መንግሥቱ ያሠራቸውን ጋዜጠኞች ባስቸኳይ እንዲለቅቅ ዛሬ ጥሪ አሰምቷል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት ባለፉ ቅርብ ሣምንታት ውስጥ አንድ የጋዜጣ ዋና አዘጋጅና ሁለት የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት ላይ ፀሐፊዎችን ማሠራቸውን፤ አራተኛው ጋዜጠኛ ላለፈው አንድ ሣምንት ያለበት እንደማይታወቅና ቤተሠቡ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሳይሆን እንማይቀር እየጠቆመ መሆኑን ሲፒጄ አመልክቷል፡፡

በመገናኛ ብዙኃን ላይ ከባድ ቁጥጥር እየተደረገ ያለው ብዙዎች ከታሠሩና መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ በኋላ መሆኑን የዛሬው የጋዜጠኞች ደኅንነት ተሟጋቹ ቡድን መግለጫ ይናገራል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች አዋጁ ከወጣ ወዲህ ከአሥራ አንድ ሺኽ በላይ ሰዎችን ማሠራቸውን ያስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የአፈፅፀም መርማሪ ቦርድ ሊቀ መንበር አቶ ታደሠ ሆርዶፋ በቅርቡ በቴሌቪዥን ቀርበው መናገራቸውን የሲፒጄ መግለጫ አስታውሷል፡፡

“መንግሥት የተቃውሞ ሰልፎችን ለመግታት እየወሰደ ያለው እርምጃ በሀገሪቱ መረጋጋትን አያመጣም” ሲሉ የሲፒጄ የአፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ አንጄላ ኲንታል ዛሬ ከኒው ዮርክ ፅሕፈት ቤታቸው ተናግረዋል፡፡

በዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት አምደኞች ላይ የሚፈፀመው ተደጋጋሚ አሥራትና ፍርድ ቤት ማመላለስ በግልፅ የሚያሣየው ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የተቀሩትን ነፃ ጋዜጠኞች ለማስፈራራት ነው ሲሉም ኲንታል አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎች ባለፈው ዓመት ጥቅምት ውስጥ በበታች ፍርድ ቤት የቀረበለትን የዞን ዘጠኝ ፀሐፊዎችን የሚመለከት አቤቱታ ከትናንት በስተያ ባስቻለው ችሎት እንደገና ማየት ጀምሯል፡፡

የሽብር ክሥ የተመሠረተባቸው ጋዜጠኞች በፍቃዱ ኃይሉ፣ ናትናዔል ፈለቀ፣ አቤል ዋበላና አጥናፍ ብርሃኔ ናቸው፡፡

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን እንድትፈታ ሲፒጄ ጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:54 0:00

XS
SM
MD
LG