ማክሰኞ, ማርች 31, 2015 የአካባቢው ጊዜ 12:41

ዜና

ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ ወኅኒ ውስጥ አረፉ

ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ
ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ ወኅኒ ውስጥ አረፉ
ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ ወኅኒ ውስጥ አረፉi
|| 0:00:00
...    
🔇
X

የሽብር ክሥ ተመሥርቶባቸው የዕድሜ ልክ እሥራት የተፈረደባቸው ኢንጂነር ተስፋሁን ጨመዳ ለሰባት ዓመታት እሥር ላይ ከቆዩ በኋላ እዚያው ወኅኒ ውስጥ ማረፋቸውን ቤተሰቦቻቸው ለቪኦኤ ገለፀዋል፡፡

ፖሊስ የሰጠውን ማስረጃ አይተናል ያሉት እስከፍርዱ ድረስ ከይግባኝ በፊት ቆመውላቸው የነበሩት ጠበቃ አቶ ጥላሁን ታደሰ ኢንጂነር ተስፋሁን ያረፉት ባለፈው ዓርብ ሌሊት መሆኑን አመልክተው የፖሊሱ መረጀ እራሣቸውን ማጥፋታቸውን እንደሚጠቁም ጠቁመዋል፡፡

ኢንጂነር ተስፋሁን እራሣቸውን አጥፍተዋል የሚለውን መግለጫ ለማመን እንደሚቸገሩ የሚናገሩት አቶ ጥላሁን ታደሰ ሕክምና እንዲደረግላቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ እንደነበረና የጠየቁትን አለማግኘታቸውን እንደሚያውቁ፤ ከእህታቸው ጋርም በማግስቱ ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘው እንደነበረ ቤተሰብ እንደነገራቸው ገልፀዋል፡፡

ከወኅኒና ሌሎችም ባለሥልጣኖች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የተደረገው ጥረት ለዛሬ ባይሳካም ሙከራችን ይቀጥላል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
ይህ ፎረም ተዘግቷል
አስተያየቶች
     
እዚህ ፎረም ላይ የሠፈረ አስተያየት የለም፤ ያውጡና የመጀመሪያው ይሁኑ