በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አባል የሆነችዉ አስፈላጊ መስፈርቶችን በማሟላትዋ ነዉ ተባለ


 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት
የኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ሆና መመረጥዋ ሲቀርቡብን የነበሩ ክሶችንና ዉንጀላዎችን ዉድቅ ያደረገ ነዉ ሲል የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታዉቋል።

የሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ቃል አባይ አቶ ዲና ሙፍቲ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሰጡት ቃል ኢትዮጵያ አባል ሆና የተመረጠችዉ አስፈላጊ መስፈርቶትን በማሟላትዋ ብለዋል። ከአንድ መቶ ዘጠና ስምንት አገሮች አንድ መቶ ሰባ ስምንቱ ኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ምክር ቤቱ አባል እንድትሆን መደገፋቸዉ ዓለም አቀፍ ድጋር እንዳላት ያመለክታል ሲሉ አክለዋል።

በሌላ በኩል የተቃዋሚዉ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ምክትል ሊቀመንበርና ቃል አቀባ ዶክተር በየነ ጴጥሮስ በስብአዊ መብቶች ጥሰት የምትታወቅ አገር ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክር ቤት አባል ሆና መመረጥዋ እኛን ብታ ሳይሆን ለመብት የሚቆረቆሩ የሰብአዊ ድርጅቶችን ጭምር ነዉ ብለዋል።

የኢትዮጵያን መንግስት የምክር ቤት አባልነቱን ለፖሮፓጋንዳ ለመጠቀም ከሆነም ለኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ጉዳት በመሆኑ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በእርምጃዉ ትልቅ ስህተት ማድረጉን መረዳት ይኖርበታል ሲሉ ተናግረዋል።

please wait

No media source currently available

0:00 0:06:24 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
XS
SM
MD
LG