ሰኞ, ግንቦት 04, 2015 የአካባቢው ጊዜ 17:02

መንግሥት በሁከቱ ሰማያዊ ፓርቲና ግንቦት ሰባትን ይከስሳል

Ethiopia-Protest

24.04.2015 03:08
ሰማያዊ ፓርቲ ክሡን አስተባብሏል፡፡ አርበኞች-ግንቦት ሰባት ግንባር በሰልፈኞቹ ላይ የተፈፀመውን ድብደባ አውግዟል፡፡ “ይህንን ሥርዓት ለማስወገድ የሚካሄድን ማንኛውንም እንቅስቃሴ እንደግፋለን” ብሏል፡፡ ሊብያ ውስጥ የኢትዮጵያዊያኑ የዛሬ ውሎ ምን ይመስል እንደነበረ ይዘናል፤ ከተገደሉት ኢትዮጵያዊያን መካከል የአንዱን ቤተሰብ አነጋግረናል፡፡ ኢትዮጵያ ዛሬም ኀዘን ላይ ነች፡፡ ተጨማሪ

ኢትዮጵያ ኀዘን ላይ ነች

የእሥልምና መንግሥት ነኝ በሚለው የሽብር ቡድን ሊብያ ውስጥ 29 ኢትዮጵያዊያንና አንድ ኤርትራዊ መገደላቸውን ኢትዮጵያዊያንና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እያወገዙ ነው፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቻይና አዲስ አበባ በረራ መስተጓጎል

ከደቡባዊ ቻይናዪቱ ጓንዡ አይሮፕላን ጣቢያ ወደ አዲስ አበባ ለመብረር የተነሣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አይሮፕላን በመንገዱ ጣልቃ ሁለት ጊዜ ማረፉ ተገልጿል፡፡

ደቡብ አፍሪካ ያሉ ኢትዮጵያዊያንና ሌሎችም መጤዎች ጥቃት እየተፈፀመባቸው ነው

በደቡብ አፍሪካይቱ ደርባን ከተማ ካለፈው ሣምንት ማብቂያ ጀምሮ በውጭ ሀገር ዜጎች ላይ በደረሱ ጥቃቶች ቢያንስ አምስት ሰው መገደሉን የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ዮናስ ቢሆነኝ - ‘ያልተዘፈነለት ጀግና’

ዮናስ ቢሆነኝ በምዕራባዊ አሜሪካይቱ ዋሺንግተን ግዛት ሲያትል ከተማ ውስጥ የመኪና መጠገኛ ጋራዥ አለው። ይሄ በራሱ አንድ ስኬት ነው። በባዕድ አገር የራስን ድርጅት አቋቁሞ የሥራ ባለቤት፣ የሥራ ፈጣሪ መሆንና፣ ለሌሎችም መትረፍ!

ሲፆሙ ጤናዎ ይበዛል፤ ዕድሜዎ ይረዝማል

አመጋገብዎን ያስተካክሉ፡፡

የቪኦኤን የቅዳሜ ምሽት የፋሲካ ልዩ ዝግጅት ያዳምጡ

ለክርስትያን ምዕመናን፤ እንኳን ለብርሃነ-ትንሣዔው አደረሣችሁ፤ ቪኦኤ

ለኅዳሴ ግድብ ግንባታ ዓለምአቀፍ አማካሪ ተመረጠ

የሕዳሴን ግድብ እንዲያጠኑ ሁለት ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች መመረጣቸውን ትላንትናና ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ስብሰባ የተቀመጡ የኢትዮጵያ የግብፅና የሱዳን ተወካዮች ገልፀዋል።

የመን ያሉ ኢትዮጵያዊያን የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው

ወደየመን የሚገቡ ፍልሰተኞች ቁጥር ቀንሷል፡፡

ከእርሻ እስከ ጉርሻ - የምግብዎን ደኅንነት ይጠብቁ

የዓለም የጤና ድርጅት መጋቢት 29 የሚውለውን የዘንድሮን የዓለም የጤና ቀን አስቦ የሚውለው ለምግብ ደኅንነት ትኩረት ሰጥቶ ነው፡፡

ቲቢ እየተሸነፈም፤ እያስፈራራም ነው

የዓለም አቅጣጫ የቲቢን መዛመት ማቆም መሆኑን አንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሥራ ኃላፊ አስታወቁ፡፡

በአባይ አጠቃቀም ጉዳይ የመርኅ ስምምነት ተፈረመ

የምሥራቅ ናይል ተፋሰስ አካል በሆኑት በኢትዮጵያ፣ በግብፅና በሱዳን መካከል የአባይ አጠቃቀምና የታላቁ ኅዳሴ ግድብ የመርኅ ስምምነት ዛሬ ተፈርሟል፡፡

አሜሪካ ከእሥልምና ጋር እየተዋጋች አይደለችም - ፕሬዚዳንት ኦባማ /ውይይት በቪኦኤ/

በዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት ዋሺንግተን ዲሲ ላይ በተዘጋጀው ዓለምአቀፍ ስብሰባ ላይ ከአቶ ተሾመ ብርሃኑ (ከኢትዮጵያ)ና ከዶ/ር አሕመድ ሞኤን (ዋሺንግተን ዲሲ) ጋር የተካሄደ ውይይት፤ ክፍል አንድ እና ሁለት፡፡

ኢትዮጵያዊያን የኢቦላ ዘማቾች ሥምሪት እየጠበቁ ነው

በየሄዱባቸው ሃገሮች የሁለት ሣምንት ሥልጠናቸውን አጠናቅቀዋል፡፡

ኢቦላና ኢትዮጵያ

ወደ ምዕራብ አፍሪካ የዘመቱት የጤና ባለሙያዎች ሲመለሱ የሃያ አንድ ቀናት ኳራንታይን ላይ እንደሚቀመጡ (ተነጥለው እንደሚቆዩ) ተገልጿል፡፡ እስከ ዛሬ በኢቦላ የተጠረጠረ ሰው ከውጭ ከገባ መንገደኛም ሆነ ኢትዮጵያዊ እንደሌለ የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡