በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠቅላይ አቃቤ ህግ ባር በምክር ቤቱ ኮሚቴ ፊት ቀረቡ


የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢል ባር በተወካዮች ምክር ቤቱ የህግ ጉዳዮች ኮሚቴ ፊት ቀርበው መልስ ሲሰጡ /ማክሰኞ፤ ሐምሌ 21/2012 ዓ.ም./
የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢል ባር በተወካዮች ምክር ቤቱ የህግ ጉዳዮች ኮሚቴ ፊት ቀርበው መልስ ሲሰጡ /ማክሰኞ፤ ሐምሌ 21/2012 ዓ.ም./

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢል ባር በተወካዮች ምክር ቤቱ የህግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ፊት ቀርበው ተጠይቀዋል።

ጠቅላይ አቃቤ ህጉ በዚህ የትናንት የምክር ቤት ውሏቸው ወቅት ባለፉት ሁለት ወራት ሰልፎችና ሁከት ወዳልተለያት የኦሬገን ግዛቷ ፖርትላንድ ከተማ “ፌደራል ኃይሎች መግባታቸው አግባብ ነው” ሲሉ በፕሬዚዳንቱ ውሣኔ ላይ ከዴሞክራቲክ እንደራሴዎች የተነሣውን ተቃውሞ ተከላክለዋል።

ዴሞክራቲክ እንደራሴዎቹ ጠቅላይ አቃቤ ህጉ “የህግ የበላይነትን ከማስከበር ይልቅ ለፕሬዚዳንቱ ያላቸውን ታማኝነት ለመግለፅ ቅድሚያ ሰጥተዋል” ሲሉ ይወነጅሏቸዋል።

ባለፈው ዓመት ውስጥ ቢል ባር ይዘዋቸዋል በሚባሉ ሌሎችም ጉዳዮች ላይ ጥያቄዎች ቀርበውላቸዋል፤ ሙሉ ቀን በዘለቀው የተካረረ ንግግር መልስና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ጠቅላይ አቃቤ ህግ ባር በምክር ቤቱ ኮሚቴ ፊት ቀረቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:31 0:00


XS
SM
MD
LG