No media source currently available
በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ከሞት የተረፉ ፍልሰተኞችን የጫነው የኢጣልያ ባሕር ኃይል መርከብ፣ ትናንት እሑድ ነው ረጅዮ ባላብርያ ወደብ ላይ የደረሰው። የሜዲትሬንያንን ባሕር ለማቋረጥ ሲሞክሩ ሕይወታቸውን ያጡ የ45 ሰዎች አስከሬንም አብሮ ተጭኗል። ከሞት የተረፉትና ብዙዎቹ ነጭ የለበሱት ፍልሰተኞች ከመርከቧ ሲወርዱ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ሠራተኞች ተቀብለዋቸዋል።