በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለዶናልድ ትረምፕ ክስ ሂደት ከሕዝብ የተውጣጡት ዳኞች ተሰይመዋል


የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ
የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ

በቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ላይ ወሲባዊ ግንኙነት ነበረን ያሉ ሴቶች ጉዳይ አደባባይ እንዳይወጣ ለማሳፈን መደለያ ከፍለዋል ከተባለው በተያያዘ ለቀረበው ክስ የተመረጡት 12 ከህዝብ የተውጣጡ ዳኞች ትላንት ሐሙስ በኒው ዮርኩ ፍርድ ቤት ተሰይመዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ በነበሩ ግለሰብ ላይ በፍርድ ቤት የወንጀል ክስ ሲቀርብ የመጀመሪያ ለሆነው ክስ የተመረጡት ሰባት ወንዶች እና አምስት ሴቶች ናቸው። ከሕዝብ የተውጣጡት ዳኞቹ 45ኛው የአሜሪካ ፕሬዚደንት ለፕሬዚደንትነት ካበቃቸው የምረጡኝ ዘመቻ ቀደም ብሎ "በትዳራቸው ላይ ወሲባዊ ግንኙነት ፈጽመናል" ብለው ለተናገሩ ሁለት ሴቶች አፍ ማዘጊያ መከፈሉን ሸሽገዋል በሚል የቀረባበቸውን ክስ ያደምጣሉ።

አቃቤ ሕግ ትረምፕ ከስምንት ዓመታት በፊት ፕሬዚደንታዊ ምርጫው ዋዜማ ላይ ለስማቸው ጥሩ ያልሆነውን መረጃ ከመራጮች ለመደበቅ ሞክረዋል ሲሉ ወንጅለዋቸዋል።

በመጪው ምርጫ በድጋሚ ለመመረጥ የቀረቡት ትረምፕ በበኩላቸው ከሁለቱ ሴቶች ጋር "ግንኙነት ኖሮኝ አያውቅም" ብለው አስተባብለዋል። ሌሎቹንም ከአንድ ዓመት በፊት የቀረቡባቸውን 34ቱንም ወንጀሎች አልፈጸምኩም ብለዋል።

የቀድሞው ፕሬዚደንት በቀረቡባቸው ክሶች ጥፋተኛ ከተባሉ እስከ አራት ዓመት የሚደርስ እስራት ቅጣት ሊያስወስንባቸው ይችላል። የኒው ዮርክ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሁዋን ሜርቻን ስድስት ሳምንታት ሊወስድ የሚችለው የፍርድ ሂደት ግራ ቀኝ ክርክር የፊታችን ሰኞ ሊጀመር እንደሚችል ገልጸዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG