በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓለም አቀፍ ሽያጭ በመቀነሱ ተስላ ከ10 በመቶ በላይ ሠራተኞቹን ሊያሰናብት ነው


ፎቶ ፋይል፦ የተስላ አርማ
ፎቶ ፋይል፦ የተስላ አርማ

የኤሌክትሪክ መኪናዎችን በማምረት የሚታወቀው የአሜሪካው ተስላ ኩባንያ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ከ10 በመቶ በላይ ሠራተኞቹን ሊያሰናብት መሆኑን፣ ድርጅቱ ለሠራተኞቹ ባሰራጨው የውስጥ ደብዳቤ አሳውቋል። ሮይተርስ ሰኞ እለት በተመለከተው ደብዳቤ ድርጅቱ በሽያጭ መውደቅ እና በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የዋጋ ንረት ምክንያት ችግር ውስጥ መግባቱን አመልክቷል።

ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን መኪናዎች በብዛት በመሸት በዓለም ትልቁ የመኪና አምራች የሆነው ተስላ እ.አ.አ እስከ ታኅሳስ 2023 ዓ. ም መጨረሻ በዓለም ዙሪያ ከ140 ሺህ በላይ ሠራተኞች እንደነበሩት የድርጅቱ ዓመታዊ ሪፖርት ያሳያል። አሁን በሚወስደው ርምጃ የትኞቹ ሥራዎች እንደሚነኩ በደብዳቤው ግልፅ አላደረገም።

በካሊፎርኒያ እና ቴክሳስ ውስጥ ያሉ አንዳንድ ሥራተኞች ከሥራ መሰናበታቸውን የሚያሳይ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ግን፣ ጉዳዩን በቅርበት የሚያቁ እና ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ አስተያየት ሰጪ ለሮይተርስ ገልጸዋል።

"ድርጅቱን ለቀጣይ እድገት በምናዘጋጅበት ምዕራፍ፣ ወጪ ለመቀነስ የሚረዳንን ሁሉንም የኩባንያውን ገፅታዎች መመልከት እና ምርታማነት መጨመር አስፈላጊ ነው" ሲሉ የተስላ ባለቤት እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኤሎን መስክ ለሠራተኞች በተሰራጨው ደብዳቤ ላይ አስፍረዋል።

ደብዳቤው አክሎ "ይህን ለማድረግ በምናደርገው ጥረት፣ ድርጅቱ ላይ ጥልቅ ግምገማ አካሂደን በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ሰራተኞቻችን 10 ከመቶውን ለማሰናበት ከባድ ውሳኔ ላይ ደርሰናል" ብሏል።

በጉዳዩ ላይ ተስላ ምላሽ እንዲሰጥ የተደረገው ጥረት አለመሳካቱን ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG