በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምርጫ በተቃረበባት ደቡብ አፍሪካ የፓርቲዎች መካሰስ ቀጥሏል


ፎቶ ፋይል፦ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ሰሪል ራማፎሳ ኬፕ ታውን እአአ የካቲት 8/2024
ፎቶ ፋይል፦ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ሰሪል ራማፎሳ ኬፕ ታውን እአአ የካቲት 8/2024

በደቡብ አፍሪካ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ያለው ውጥረት እየተባባሰ ባለበት ወቅት፣ በአንድ ተቃዋሚ ፓርቲ የተለቀቀውና ሰንደቅ ዓላማ ሲቃጠል የሚያሳየው ማስታወቂያ “የሃገር ክህደት” ነው ሲሉ የሃገሪቱ ፕሬዝደንት ሰሪል ራማፎሳ ተናገሩ።

ምርጫው ሶስት ሳምንታት በሚቀረው በዚህ ወቅት ሰኞ ዕለት ‘ዲሞክራሲያዊ ኅብረት’ የተባለው ፓርቲ በለቀቀው የምርጫ ዘመቻ ማስታወቂያ፣ ሰንደቅ ዓላማ ሲቃጠል ማካተቱ፣ ገዢው የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ሥልጣን ይዞ መቀጠሉ የደቀነውን አደጋ ለማመልከት ምሳሊያዊ ሆኖ እንደቀረበ አስታውቋል።

በሎምፖፖ ግዛት ጉብኝት ላይ ያሉት ሰሪል ራማፎሳ፣ ድርጊቱ “የሃገር ክህደት ነው፤ የሃገሪቱ የአንድነት ምልክት የሆነውን ሰንደቅ ዓላማ ማራከስ እጅግ አሳፋሪ የፖለቲካ ድርጊትም ነው” ሲሉ ተደምጠዋል።

‘ዲሞክራሲያዊ ኅብረት’ ፓርቲ ከአምስት ዓመታት በፊት በተደረገው ምርጫ ሁለተኛውን የድምፅ ብዛት ያገኘ ሲሆን፣ ከኦስት ሳምንታት በኋላ በሚደረገው ምርጫ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ከ 30 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ግዜ የያዘውን የበላይነት ሊያጣ እንደሚችል የሕዝብ አስተያየት መለኪያዎች በማመልከት ላይ ናቸው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG