በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ አፍሪካ አውቶብስ ተገልብጦ 45 ሰዎች ሞቱ

የፈረንጆች ፋሲካ ለማክበር ወደ አንድ ቤተክርስቲያን ሲያቀኑ የነበሩ አማኞች ይጓዙበት የነበረው አውቶብስ በተራራማ አካባቢ ከነበረው ድልድይ ላይ ስቶ 50 ሜትር ርቀት ካለው ገደል ውስጥ ሲወድቅ በእሳት ተቀጣጥሏል፤ ሊምፖፖ፣ ደቡብ አፍሪካ እአአ መጋቢት 28/2024
የፈረንጆች ፋሲካ ለማክበር ወደ አንድ ቤተክርስቲያን ሲያቀኑ የነበሩ አማኞች ይጓዙበት የነበረው አውቶብስ በተራራማ አካባቢ ከነበረው ድልድይ ላይ ስቶ 50 ሜትር ርቀት ካለው ገደል ውስጥ ሲወድቅ በእሳት ተቀጣጥሏል፤ ሊምፖፖ፣ ደቡብ አፍሪካ እአአ መጋቢት 28/2024

እሁድ የሚውለውን የፈረንጆች ፋሲካ ለማክበር ወደ አንድ ቤተክርስቲያን ሲያቀኑ የነበሩ አማኞች ይጓዙበት የነበረው አውቶብስ ገደል ውስጥ ሲገባ 45 ሰዎች ሞተዋል። ከአደጋው የተረፈው አንድ የ8 ዓመት ልጅ ሲሆን፣ በሕክምና ላይ ይገኛል ተብሏል።

ሊምፖፖ የተባለው የአካባቢ አስተዳደር እንዳስታወቀው፣ አውቶብሱ በተራራማ አካባቢ ከነበረው ድልድይ ላይ ስቶ 50 ሜትር ርቀት ካለው ገደል ውስጥ ሲወድቅ በእሳት ተቀጣጥሏል።

ተጓዦቹ ከቦትስዋና የተነሱ ሳይሆኑ እንዳልቀረና ሞሪያ በተባለ ሥፍራ በሚከናወንና በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች በሚሳተፉበት ዓመታዊ የፋሲካ በዓል የእምነት ሥነ ስርዓት ላይ ለመታደም እያቀኑ እንደነበር የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል። ሥነ ስርዓቱ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኋላ ሲካሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነም ታውቋል።

አንዳንዶቹ ሰለባዎች መለየት በማይቻል ሁኔታ የተቃጠሉ ሲሆን፣ ሌሎቹ ደግሞ ከአውቶብሱ ተፈናጥረው ወደ ገደል ወድቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG